የተቆለፈበት ቁልፍ

Book የተቆለፈበት ቁልፍ

የተቆለፈበት ቁልፍ

የታሪኩ ዋነኛ ገጸባህርያትን ተከትሎ በብዙ ሰዎች እና ቤተሰቦች ዙሪያ የሚያጠነጥነው ይህ ታሪክ በኢትዮጵያና በአሜሪካ የተከወነ ሲሆን በውስጡም ፍቅርና-ቅናት፣ ክፋትና-ደግነት፣ ጭካኔና-ርህራሄ፣ ድህነትና-ስኬት ይንጸባረቁበታል፣ ይፈራረቁበታል። ከገጠር እስከ ከተማ፣ ከቤት ቤት ይዞራል፧፧ በታሪኩ ዉስጥ የተቆላለፉ ጉዳዮች እስኪፈቱ አንባቢ ከራሱ አእምሮና አስተሳሰብ ጋር ፊትለፊት ይላተማል፧፧ የሰው ኑሮው፣ የቤተሰብ ደረጃውና የአገር ልኩ ከአስተሳሰብ እንደማይዘልና አስተሳሰብም ሳይቀየር የሰውን ኑሮ የሀገርንም መልክ መቀየር እንደማይቻል ማሳየት ብቻ ሳይሆን መንገድና አቅጣጫንም ይጠቁማል።
Авторы

ዘሪሁን አስፋው

No Image

ምህረት ደበበ

No Image